ስለተቋሙ

ሰርድሚል ተቋም በሰርድሚል የተቋቋመ የሰርቴፊከት ፕሮግራም ነው አላማውም የአገልግሎት ትምህርት ለሚፈልጉ ሁሉ ነጻ የመጽሐፍ ቅዱስና የስነ መለኮት ስልጠና በሰሚኔሪ ደረጃ መስጠት ነው ፕሮግራሙ የተቀረጸው ከሕይወትና ከአገልገሎት ልምዶችም መማማር በሚቻልባቸው በትንሽ ቡድኖች ለማስተማር ታቅዶ ነው ይህንንም የሚያስፈጽመው እዛው አብሯቸው ያለው የራሳቸው አሰልጣኝ ነው

ሰርድሚል ተቋም በሰርድሚል የተቋቋመ የሰርቴፊከት ፕሮግራም ነው አላማውም የአገልግሎት ትምህርት ለሚፈልጉ ሁሉ ነጻ የመጽሐፍ ቅዱስና የስነ መለኮት ስልጠና በሰሚኔሪ ደረጃ መስጠት ነው ፕሮግራሙ የተቀረጸው ከሕይወትና ከአገልገሎት ልምዶችም መማማር በሚቻልባቸው በትንሽ ቡድኖች ለማስተማር ታቅዶ ነው ይህንንም የሚያስፈጽመው እዛው አብሯቸው ያለው የራሳቸው አሰልጣኝ ነው

የተቋሙ ፕሮግራም በነጻ የሚሰጥ ሲሆን የትምህርት ደረጃ ገደብ ሳይጣልበት ለሁሉም ሰው ክፍት ነው በተጨማሪም ደግሞ ሰልጣኞች በሚመቻቸው አይነት ሁኔታ ትምህርቱን ለመስጠት በብይነ መረብ ወይም ከብይነ መረብ ውጭ ለማድረግ ነጻነት አለው ፕሮግራሙ ለተማሪዎች የግልና የአገልገግሎት ልምዳቸው ከፍተኛ ዋጋ እየሰጠ ተማሪዎችን በመጽሐፍ ቅዱስና በስነ መለኮት ለማሰልጠን በከፍተኛ ጥራት የተቀረጸውን የሰርድሚል ስርአተ ትምህርት ይጠቀማል ይህንን የሚናደርገው የመማር ማስተማር ሂደቱን በማቀናጀትና በቡድን በሚማሩበት ጊዜ መጠቀም ያለባቸውን አስፈላጊ ዶክመንቶችን በማዘጋጀት ነው

የሰርድሚል ተቋም ተማሪዎችንና አሰልጣኙን የያዘ ብዙ የመማር ማስተማር ቡድኖችን ለመፍጠር ከቤተክርስቲያናትና ከክርሰቲያን መሪዎች ጋር አብሮ ይሰራል እነዚህን የአካባቢ መሪዎችን እኛ የተቋሙ አሰልጣኞች እንላቸዋለን የኛ ስርአተ ትምህርት የተቀረጸው እነዚህ አሰልጣኞች ትምህርቱን በማዘጋጀትና በማስተማር እንዳይደክሙ ይልቁን በተግባራዊነቱ ላይ የበለጠ ማተኮር እንዲችሉ ተደርጎ ነው እያንዳንዱ ለመማር የሚፈልግ ቡድን የራሱን አሰልጣኝ የማግኘት ሃላፊነት አለበት ይህም ደግሞ በተለይ ከዚያው አጥቢያ ቤተክርስቲያን ወይም ደግሞ ከቤተክርሰቲያናት ህብረት ወይም ከሰርድሚል አጋሮች ብሆን ይመረጣል

ብይነ መረብ የሚጠቀሙ ተማሪዎች በሰርድሚል ዌብሳይት በኩል የተቋሙን የትምህርት ዶክመንቶችን በቀጥታ ማግኘት ይችላሉ በሌላ በኩል ደግሞ ብይነ መረብ የማይጠቀሙ ተማሪዎች ከተቋሙ microSD (ማይክሮ SD) ካርድ መጠየቅ ይችላሉ

group talking and reading

የመሰረቶች ሰርቲፊከት

በመጽሐፍ ቅዱስና በስነ መለኮት አራት የመግቢያ ኰርሶችን ያየዘ ነው

መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረቶች – ከወንጌል ስርጭት ባጅ ጋር
መንግስት ቃል ኪዳናትና የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና መንግስትና ቃል ኪዳን በአዲስ ኪዳን

ስለ መለኮታዊ መሰረቶች – ከጸሎት ባጅ ጋር
የሐዋርያት የሃይማኖት መግለጫ ና የራስን ስነ መለኮት መሰነድ

የብሉይ ኪዳን መሰረቶች – ከደቀ መዝሙርነት ባጅ ጋር
ፔንታቱክ

የአዲስ ኪዳን መሰረቶች – ከስብከትና/ማስተማር ባጅ ጋር
ወንጌላት ና የሐዋርያት ስራ

ምስክር ወረቀት በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

ይህ አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሶችን ይይዛል

የብሉይ ኪዳን ትረካዎች – ከግል ጽሞናዎች ባጅ ጋር
መጽሐፈ ኢያሱ ና መጽሐፈ ሳሙኤል

የብሉይ ኪዳን ነቢያት – ከቤተሰብ ሕይወት ባጅ ጋር
ትንቢተ ሆሴዕ እና እርሱ ነቢያትን ሰጠን

የጳውሎስ መልእክቶች ጥናት – ለራስ ከመጠንቀቅ ባጅ ጋር
የጳውሎስ ስነ መለኮት ዋናው ሀሳብ እና የጳውሎስ የእስር ቤት መልእክቶች

የአዲስ ኪዳን መልእክቶች – ከቻርተር ባጅ ጋር
የዕብራውያን መጽሐፍ የያዕቆብ መልእክት እና የዮሐንስ ራዕይ

የመጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎም – ከባለ አደራነት ባጅ ጋር
እርሱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻህፍት ሰጠን- የትርጉም መሰረቶች

students learning together

ምስክር ወረቀት በስነ መለኮት ጥናት

ይህ አምስት የስነ መለኮት ኮርሶችን ይይዛል

ዶክትሪን ስለ እግዚአብሔር አብ ከአገልግሎትና ህይወት ጥበብ ባጅ ጋር
በእግዚአብሄር እናምናለን እና ስልታዊ ስነ መለኮት መሰነድ

ስለ ክርስቶስ ማንነት ጥናት ከአገልግሎትና ህይወት ጥበብ ባጅ ጋር
በኢየሱስ እናምናለን እና መጽሀፍ ቅዱሳዊ የስላሴ ዶክትሪን

ስለመንፈስ ቅዱስ ጥናት ከአገልግሎትና ህይወት ጥበብ ባጅ ጋር
በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እና መጽሀፍ ቅዱሳዊ ስነ መለኮት መመስረት

አንትሮፖሎጂ እና የዘመን መጨረሻ ከአገልግሎትና ህይወት ጥበብ ባጅ ጋር
ሰው ምንድነው? እና መንግስትህ ትምጣ : የዘመን መጨረሻ ዶክትሪን

መጽሀፍ ቅዱሳዊ ግብረ ገብ ከአገልግሎትና ህይወት ጥበብ ባጅ ጋር
መጽህፍ ቅዱሳዊ ውሳኔዎችን ማድረግ

እነዚህን ሶስቱን ሰርቲፊከቶችን ሲጨርሱ
ተማሪዎች ክርስቲያናዊ አገልግሎት ዲፕሎማ ያገኛሉ

ተማሪ መሆን ይፈልጋሉ?

አስፈላጊ መስፈርቶች- ሁለት መስፈርቶች ብቻ ናቸው ያሉት የመጀመሪያው ከሚማሩት አንዱ መሆን ሁለተኛው እያንዳንዱ ተማሪ በተቋሙ የሚማረውን ትምህርት በስራ ላይ ማዋል እንዲችል  በራሱ ቤተክርሰቲያን ድርጅት ወይም ማህበረሰብ ውስጥ በአገልግሎት ተሳታፊ እንዲሆን እንፈልጋለን

እንዴት መመዝገብ እችላለሁ?
በዚህ ገጽ ላይ ከላይ በቀኝ በኩል ያለውንና አንተን ወደ ተቋሙ ብይነ መረብ ትምህርት መስጫ ስስተም የሚያደርሰውን በብጫ የተጻፈውን CLASSROOM LOGIN የሚለውን ቁልፍ ጫን በል ከዚያም የተማሪ አካውንት ለመፍጠር username እና password ስጥ የሚል ጽሁፍ ይወጣል ይህንን ስታደርግ ጨርሰሃል ማለት ነው ከዚያ በኋላ ለእያንዳንዱ ኮርስ ለመመዝገብ ኮምፒውተሩ የሚመራህን ጽሁፍ መከተል ያስፈልጋል

አሰልጣኝ እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
አሰልጣኝ ለማግኘት ከሁሉ የተሻለው መንገድ የቤተክርስቲያንህ የአገልግልት ተቋምህ ወይም የማህበረሰቡ መሪዎች ልረዱህ የሚችሉ ከሆነ ከነርሱ ጋር መነጋገር ነው አብዛኛውን ጊዜ ቤተክርስቲያናት በመሪዎች ስልጠና ጉዳይ ለመተባበር እድሉን ካገኙ ደስተኞች ናቸው የበለጠውን ደግሞ የተሻለው ለዚህ  አገልግሎት ራሱን የሚሰጥ ካለ ለማየዬት ከቤተክርስቲያንህ መጋቢ ሌሎች መሪዎች ጋር ወይም በማህበረሰብህ ውስጥ ከሚገኘው ላንተ ከሚቀርበው ጓደኛህ ጋር መነጋገር ነው

በራሴ ማህበረሰብ ወይም ቤተክርስቲያን በዚህ አገልግሎት ከኔ ጋር መሳተፍ የሚፈልግ ሰው ካላገኘሁስ?
አንድ ሰው ተማሪ ሆኖ ሳለ ባንተ ቡድን ውስጥ ያለ የሚታስታውሰው ሰው አለ? ያ ሰው ተማሪ ሆኖ የሰርቲፊከት ፕሮግራሙን እየሰራ እያለ ደግሞ ማሰልጠን ይችላል ተቋሙ የተቋቋመው አንተ ብዙ ልምድ ባይኖርህም እንኳን አሰልጣኝ መሆን በሚያሰችል አይነት ሁኔታ ነው እኛ በአሰልጣኞች ገጽ ላይ አሰልጣኝ ለመሆን የሚያስፈልገውን መረጃ ሁሉ እንሰጣለን

በዚህ ሁሉ ከኔ ጋር መሆን የሚችል ሰው ማግኘት ካልቻልኩስ?
በአካባቢህ አሰልጣኝ መሆን የሚችል ወይም በቡድኑ ውስጥ ካንተ ጋር ለመሆን ፈቃደኛ የሚሆን ሰው ማግኘት እንድትችል እኛ ልንረዳህ ስለሚንችል እኛን ሊታገኘን ትችላለህ [email protected]

ተማሪ ስለመሆን የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክህን የተማሪ መግለጫ (ኦሪኤንተሽን) ማኗል ተመልከት

አሰልጣኝ መሆን ይፈልጋሉ?

የተቋሙ አሰራር የተቀረጸው ማንኛውም ሰው አሰልጣኝ መሆን እንደሚችል ተደርጎ ነው አንተ ለአገልግሎት አዲስ ወይም በጣም ትንሽ ልምድ ያለህ ብትሆንም በሌላ አንጻር ደግሞ የረጅም ጊዜ ልምድ ያለህ ብትሆንም በሁለቱም አሰልጣኝ መሆን ትችላለህ የስልጠና ዶክመንቶቻችን የውይይት መመሪያዎቻችን ባጆቻችን ሁሉ ሳምንታዊውን የትምህርት ክፍለ ጊዜና ሂደቱን በሙሉ እንዴት ማድረግ እንዳለብህ ይመሩሃል አንተ ምናልባት የአመታት የአገልግሎት ልምድ ያለህ ከሆነ ያንን ልምድህን ለማካፈል የሚያስችል ሁኔታም አለ በሌላ በኩል ደግሞ አነስ ያለ ልምድ ያለህ ከሆነም ዶክመንቱ ራሱ አንተና ተማሪዎችህ የተማራችሁትን ነገር እንዴት በስራ ላይ ማዋል እንዳለባችሁ ይመራችኋል

ለአሰልጣኝነት ለመመዝገብ ከታች ያሉትን ደረጃዎችን ተከተል የአስልጣኝነት ቅጽ ሙላ ከዚያም በብይነ መረብ ትምህርት ክፍል ለመመዝገብ LOGIN የሚለውን ቁልፍ ተጫን .

እንዴት አሰልጣኝ መሆን እችላለሁ?

አሰልጣኝ መሆን ቀላል ነገር ነው አስፈላጊ መረጃዎችን ከታች በመስጠት በዚህ ገጽ ላይ Sign up አድርግ አሰልጣኝ ለመሆን አንዴ Sign up  ካደረግክ በኋላ በሶስት መንገዶች የስልጠና ሰነዶችን ማግኘት ትችላለህ

1) የስልጠና ማኗሎቻችንን አንብብ “የአሰልጣኝ መግለጫ” እና “የተቋሙ የስልጠና  መርሆዎች” ፕሪንት አድርገህ ለራስህ ማጣቀሻ እንድሆንህ አስቀምጥ ዶክሜንቶችን መግኘት የሚትችልበት links ከዚሀ ገጽ ግርጌ ላይ ይገኛሉ ስለጠናዎቻችንን የሚትስደው በየትኛውም መንገድ ይሁን እነዚህ ሁለተ መነሎቻችን ተማሪችህን ለመምራት እንደ መመሪያ ያገለግላሉ

2) ከላይ ያለውን “የአሰልጣኝ መግለጫ” ቪዲዮ ተመልከት  ወደፊት የበለጠ የስልጠና ቪዲዎችን  ቶሎ ቶሎ እንጨምራለን

3) በየጊዜው ከሚደረጉ የሰርድሚል ስልጠናዎች አንዱን በአካል ወይም በብይን መረብ ተካፈል

ከነዚህ ውስጥ አንዱን ወይም ሁሉንም ካደረግክ በኋላ በተቋሙ የክፍል ትምህርት ዌብ ሳይት ላይ አካውንት ለመፍጠርና ስርአተ ትምህርቱን ለማግኘት በዚህ ገጽ ራስጌ ላይ የሚገኘውን Login ቁልፍ

የአሰልጣኝ ምዝገባ ቅጽ

ብዙ ስሞች ካሉ ነጠላ ሰረዝ ያስገቡ